የኢትዮጵያ ወጣቶች ተስፋ ድርጅት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተነሱ የሚሉ የጥሪ ወረቀቶችን መበተኑን አስታወቀ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ሳት ዜና:-ድርጅቱ በፎቶግራፍ አስደግፎ ለኢሳት የላከው መረጃ እንደሚያሳየው የተበተኑት ወረቀቶች ይዘት ከሞላ ጎደል ህዝቡ ለለውጥ እንዲነሳ የሚጠይቁ ናቸው። አንደኛው ወረቀት  ላይ ” የትግላችን አላማ ሀገራችንንና ራሳችንን ነጻነት ለማቀዳጀት ነው።” የሚል መልእክት የሰፈረ ሲሆን፣ በሌላ ወረቀት ላይ ደግሞ ” ትግላችን በገዛ ሀገሩ ህይወት እየጨለመበትና ተስፋ እየቆረጠ ሀገሩን ጥሎ ሲሰደድ በረሀና ባህር እየበላው ወላጅ እናቱ የት እንደወደቀ ሳታውቅ በገፍ መርገፍ የጀመረውን ወጣት ሰቆቃ ለማስቆም የሚደረግ ትግል ነው።” የሚል መልክት ቀርቧል።

“ወያኔ በቃ፣ መለስ በቃ ፣ በወያኔ ስርአት በባርነት ከማለቅ የተለየ ነገር የለምና ለነጻነትን ታገል የሚል ወረቅት በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ተለጥፎ ነበር። ከምርጫ 97 ወዲህ በመንግስትን ላይ ተቃውሞአቸውን ለመሳማት እና ለለውጥ ለመታገል የሚፈልጉ ወጣቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ይነገራል።

__________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide