ሚያዝያ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መረጃዎች እንደሚያመለክትቱት ከዚህ ቀደም በኢህአዴግ መንግስት ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ላይ ሲያርሱ የነበሩ አርሶአደሮች በሱዳን ታጣቂዎች ተኩስ የተከፈተባቸው ሲሆን፣ አርሶደሮችም ራሳቸውን በማደራጀት የአጸፋ እርምጃ መውሰዳቸው ታውቋል።
በሁለቱ ሃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ግጭቱ የረገበ ቢመስልም ውጥረቱ ግን እንዳለ ነው ይላሉ። ኢትዮጵያውያኑ ለሱዳን የተሰጠው መሬት የኢትዮጵያ መሬት ነው በማለት ተቃውሞ ያሰማሉ። የሱዳን ታጣቂዎች በኢትዮጵያውያን የእርሻ ማሳ ላይ የወሰዱትን እርምጃ በአካባቢው ሰፈሩት የመከላከያ ሃይሎች ለማስቆም ጥረት አለማድረጋቸው ኢትዮጵያውያኑን አስቆጥቷል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት “እርምጃ እንድንወስድ የመጣልን ትእዛዝ የለም” በሚል ዳር ቆመው እያዩ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።