የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቤተእስራኤላዊያኑ የተቃውሞውን ሰልፍ ያደረጉት ደማስ ፈቃደ የተባለ ቤተእስራኤላዊ  ወታደር በፖሊሶች መደብደቡን ተከትሎ ነው። አንድ ፖሊስ ወታደር ደማስን መደብደቡን የሚያሳይ በሚስጢር የተቀረጸ ቪዲዮበማህበራዊ ሚዲያዎች ይፋ ከሆነ በሁዋላ ፣ ቤተ እስራኤላውያኑ ቁጫቸውን በአደባባይ ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ ከፖሊስ ጋር ግጭት ፈጥረው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን የፈጸመውን ፖሊስ ከስራ አግዶ ክስ ሊመሰርትበት መሆኑ ታውቋል። ቤተ እስራኤላውያን በእስራኤል ፖሊሶች የተለያዩ ችግሮች እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ።