(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 28/2011) በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የህብረተሰቡ እገዛ ያስፈልገኛል ሲል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጥሪ አቀረበ ።
ከ90ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ከ523 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግም ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ትናንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ማህበሩ ባለፋት ጊዜያት በርካታ ድጋፎች ቢያደርግም የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል ብሏል።
እናም ሕብረተሱ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል ፡፡
በእለቱም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለአንድ አምቡላንስ መግዣ የሚውል የ1.2 ሚሊየን ብር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡