ኢሳት (ሰኔ 27 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አሜሪካ 33ኛ ዓመት በዓል በካናዳ ቶሮንቶ በድምቀት ተከፈተ።
ከተለያዩ የካናዳ ግዛቶች እንዲሁም ከዩኤስ አሜሪካ የተጓዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር እንደታደሙበት በተገለጸው በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያውያን በዓል፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከኢትዮጵያ ጭምር የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ መሳተፋቸውን መረዳት ተችሏል።
የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ይህ ታላቅ የኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ መድረክ፣ “የኢትዮጵያውያን ሰንደቅ አላማ በባዕድ ሃገር በድምቀት የምናውለበልብበት ዝግጅት ህይወት እናንተ ናችሁ” ሲሉ ምስጋና አቅርበዋል።