የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ እግርኳስ ቡድን በፌዴሬሽኑ ችግር ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ውጪ ሆኑ

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም በመጪው አመት ህዳር ወር ላይ በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ የእንስቶች የእግርኳስ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለውን የእጣ ድልድል ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለውን የተሳትፎ ማረጋገጫ ደብዳቤ የኢትዮጵያ እግርኳስ ማኅበር በወቅቱ ባለመላኩ ምክንያት የአፍሪካ እግርኳስ ማኅበር የኢትዮጵያ ሴቶች እግርኳስ ቡድን ሉሲዎችን ከምድብ ድልድል እጣ ውጪ መሆናቸውን አስታውቋል።
የአፍሪካ እግርኳስ ማኅበር ካፍ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የማጣርያ ጨዋታዎቹን ድልድል ያወጣ ሲሆን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በማጣርያው ድልድል ላይ አለመካተቱ የሚያሳየው የኢትዮጵያ እግርኳስ ማኅበርን ጨምሮ በስፖርቱ ዘርፍ በኃላፊነት የተቀመጡት ሹመኞች የስራ ድራሻቸውን የማያውቁ፣ በሙስና ሰንሰለት የተተበተቡ፣ ሕዝባዊ ኃላፊነት የማይሰማቸው መሆናቸውን ያሳያል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ማኅበር በሁለት የቢጫ ካርድ የታገደ ተጫዋቹን በፋክስ የተላከ መልዕክት ማስተላለፍ ተስኖት ብሄራዊ ቡድኑ መቀጣቱ የቅርብ ጊዜ ት ዝታችን ነው።