የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበርኞች ግንባር ሰራዊት በወልቃይት ድል መቀዳጀቱን ገለጸ

ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 16፣ 2006 ዓ/ም በወልቃይት አድነጣ በተሰኘ ስፍራ በስርዓቱ የሚሊሻ ታጣቂ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ 18 ገድሎ ቻለው ሲሳይ  እና  ተጫነንጉሱ የተባሉ 2 ወታደሮችን መማረኩን አስታውቋል።

ሰራዊቱ ለሁለቱም ምርኮኞች ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታና ስለድርጅቱ አላማና ግብ በማስተማር እንደለቀቃቸውም ድርጅቱ ገልጿል።

ሰኔ 18-2006 ዓ/ም ደግሞ   የኢሕአግሰራዊት ከመንግስት የልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር በወልቃይት አወርቂ በተባለ ቦታ ከጠዋቱ 1ሰዓትእስከ 5 ሰዓት ለአራት ሰዓት ያህል ባካሄደው እልህ አስጨራሽ ውጊያ 36 ገድሎ አርባ ስምንት 48 ማቁሰሉንና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ከነመሰል ጥይቶቻቸውና ትጥቃቸው ጋር መማረኩን ገልጿል።

ውጊያው በተካሄደበት አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችና በ2007 ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የምርጫ ድራማ ሳቢያ ከፍተኛ እንግልትና ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኙ ወገኖች ግንባሩን እየተቀላቀሉ እንደሚገኙም ግንባሩ ለኢሳት የላከው ዜና ያመለክታል።

አርበኞች ግንባር አገኘሁ ያለውን ድል በተመለከተ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም።