ኢሳት (ነሃሴ 30 ፥ 2008)
ዛሬ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ የነበረ የኢትዮጵያና የግብጽ የአባይ ግድብ ምክክር ከጸጥታ ችግራ ጋር በተያያዘ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ የኢትዮጵያ መንግስት መወሰኑን የግብፅ ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ። ሁለቱ ሃገራት የአባይ ግድብ ግንባታ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት (በተለይ በግብፅ ላይ) የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለማስጠናት ከሁለት የፈረሳይ ኩባንያዎች ጋር ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ የፕሮጄክት ስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።
ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት ሊካሄድ የነበረው የሁለት ቀን ልዩ የምክክር መድረክ ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ለግብፅ መንግስት ጥያቄ ማቅረቡን አልሚስሪ የተሰኘ ጋዜታ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት ዝግጅቱ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍለት ጥያቄን ቢያቀርብም ተለዋጭ የጊዜ ገደብ አለማስቀመጡም ታውቋል።
በኦሮሚያና አማራ ክክሎች እየተካሄዱ ያሉ ህብዛዊ ተቃውሞዎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሊዛመቱ ይችላሉ ስትል አሜሪካ በቅርቡ ማሳበቧ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ በመዲናይቱ አዲስ አበባ ሊካሄድ የነበሩ በርካታ ሃገርና አለም አቀፍ ዝግጅቶች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲተላለፉ እየተደረገ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
የኢትዮጵያና ግብፅ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ ሊያካሄዱ የነበረው የጋራ ምክክርና የፕሮጄክት ስምምነት ለሁለት አመታት ሲካሄድ ከነበረው የሁለቱ ወገኖች ድርድር ዕልባትን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ እንደነበር የግብፅ ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
ይኸው ይግባኝ የማይኖረው የሁለቱ የፈረንሳይ ኩባንያዎች የጥናት ውጤት ከስምንት ወር በኋላ ለሁለቱ ወገኖች ድርድር አልባትን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ እንደነበር የግብፅ ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
ይኸው ይግባኝ የማይኖረው የሁለቱ የፈረንሳይ ኩባንያዎች የጥናት ውጤት ከስምንት ወር በኋላ ለሁለቱ ሃገራት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ መንግስት ኩባንያዎች የሚሰጠውን የባለሙያዎች ምክር ተከትሎ በአባይ ግድብ ግንባታ ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑን ከአንድ ወር በፊት ለግብፅ ማረጋገጡ ይታወሳል።
ሁለቱ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ጥናቱን ለማካሄድ አምስት ሚሊዮን ዩሮ (ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ) በሃገሪቱ እንደሚከፈላቸው ለመረዳት ተችሏል።