የኢትዮጲያ ሙስሊሞች በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የእስር ቤት ጉብኝት ወይም ጥየቃ ትላንት ተካሄደ

ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጲያ ሙስሊሞች በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የእስር ቤት ጉብኝት ወይም ጥየቃ ትላንት ተካሄደ ከአዲስ አበባ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ከ ፲፻ ሺህ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች በእስር ላይ የሚገኙትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ለመጠየቅ እንዲሁም ትግላቸው ሰላማዊ መሆኑን ደግሞ ለማመሳከርና ለታሰሩት ድጋፍ ለማሳየት ወደ ቃሊቲ አምርተዋል።

በእለቱ ከአራቱም የአዲስ አበባ አቅጣጫዎችን ከአጎራባች መንደሮች ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያመሩት የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትላንት ጠዋት ጀምረው በሰልፍ በመሆን መሪዎቻቸውን ለመጎብኘት ሲጠባበቁ ታይተዋል። በኢትዮጲያ የሰላማዊ ትግል ታሪክ የመጀመሪያው በሆነው በቃሊቲው የትላንቱ የሙስሊሞች ተዕይንት ኢትዮጲያውያን ክርስቲያኖችም በተልያዩ መንገዶች ድጋፋቸውን መግለፃቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በትላንቱ የቃሊቲው ትዕይንት የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ቃሊቲ ዙሪያ ያገኟቸውን ተሽከርካሪዎች ታርጋ ነቃቅለው ሲወስዱም ታይተዋል።