የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የኦጋዴንየዜናአገልግሎትን <<በመጥቀስዋጋኩሱብ>> የተሰኘውየግንባሩልሳንእንዳስታወቀው፤የመከላከያሚኒስትሩሲራጅፈርጌሳእና የደህንነትሹሙአቶጌታቸውአሰፋ – ከኦጋዴነጻነትግንባር የውጪግንኙነትሀላፊከአቶአብዲራሁምማህዲእና ከግንባሩዋናጸሀፊ ከአቶአብዲያሲንጋርበናይሮቢተገናኝተው ድርድሩንጀምረዋል።
ሁለቱምወገኖችበአብዛኞቹየድርድሩመርሆዎችላይ መስማማታቸውምተገልጿል።
በሁለቱወገኖችመካከልለአስርትኣመታትየዘለቀውግጭት በመነጋገርእንዲፈታዓለማቀፉማህበረሰብግፊትእያደረገእንደሚገኝየግንባሩዜናአገልግሎትአውስቷል።
ሁለቱወገኖችባለፈውጥቅምትወርበኬንያጀምረውትየነበረውድርድር፤የኢትዮጵያመንግስት ያቀረበውንቅድመ-ሁኔታኦብነግለመቀበልፈቃደኛባለመሆኑምክንያትመቋረጡይታወሳል።
እንዲሁም የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በተመሳሳይ መንገድ ለድርድር ናይሮቢ የሄዱትን 2 የኦብነግ ከፍተኛ አመራሮች አፍነው መውሰዳቸው አይዘነጋም።
እንደኦጋዴንዜናአገልግሎትዘገባየኦጋዴንግጭትበአፍሪካየግጭትታሪኮችረዥሙሲሆን፤እስካሁን 500 000 ሰዎችሞተዋልከሚሊዮንየሚልቁክልሉንለቀውተሰደዋል።
አንዳንድ ወገኖች ክልሉን በማስተዳደር ላይ ያሉት አቶ አብዲ ሞሃመድ ከህወሃት የጦር አዛዦች ጋር በመሆን የሚፈጽሙት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፣ የኢህአዴግን ባለስልጣናት ከማስወቀስ አልፎ በጦር ወንጀልና በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያስጠይቃቸው በመሆኑ፣ መንግስት ምናልባትም አቶ አብዲ ከስልጣን ወርደው ክልሉን የማስተዳደር ስልጣኑን ለኦብነግ መሪዎች በመስጠት የሚቀርበውን ውንጀላ ለማለዘብ ሊሞክር ይችላል ይላሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ድርጅቶች ጥንካሬ እያሰጋው የመጣው መንግስት፣ በሁሉም አቅጣጫዎች ሊሰነዘርበት የሚችለውን ጥቃት ለመቀነስ ከኦብነግ ጋር ድርድሩን ለመግፋት ሳያሳብ እንዳልቀረ አስተያየት ይሰጣሉ።
በኤርትራና በአጎራባች የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች ሃይላቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከሩ በመምጣት ላይ መሆናቸው ገዢው ፓርቲ በድንበር አካባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያጠናክር እያደረገው ነው።