ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ ከሶስት ህጻናት ልጆች ጋር ለእህቷ ስርግ ወደ ኢትዮጰያ አቅንታ የነበረችውና ላለፉት 20 ቀናት በአዲስ አበባ የቆየችው ወይዘሮ አበባ፤ ከነ ልጆቿ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ታስራ እንድታድር ከተደረገች በሁዋላ ነው ከሀገር የተባረረችው።
በእህቷ ሰርግ ላይ በርካታ ደህንነቶች ሲከታተሏት እንደነበረ የገለጸችው ወይዘሮ አበባ፤ በማግስቱ በቤተሰቦቿ ቤት ሳለች ሁለት ደህንነቶችና አራት ፖሊሶች በመምጣት ከሶስት ዓመት ህጻን ልጇ ጋር እያዋከቡ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ይዘዋት እንደሄዱና እዛ ባለ ቢሯቸው ውስጥ እንዳሰሯት ተናግራለች። ደህንነቶቹ አክለውም ፦<<ወንጀለኛ ነሽ፤ባለቤትሸ ኢሳት ላይ መስራት እስካላቆመ ድረስ ኢትዮጰያ የመኖር መብት የለሽም እንዳሏት ተናግራለች::