የኢሳትን ህልውና የማረጋገጥ ጥሪ

መጋቢት 27 ቀን 2004 ዓ/ም

የኢሳት – ማኔጅመንት

 

ኢሳት ከተቋቋመ ከዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ ህዝባችን የሞራል የገንዘብ እና የተለያዩ እርዳታዎች በማድረጉ ይህ የህዝብ አይንና ጆሮ የሆነ የሚድያ ተቋም ዛሬ የሚገኝበት ደረጃል ለመድረስ በቅቷል። ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀላሉ የማይዳፈን የተስፋ ብርሃን መፈንጠቅ አስችሏል።

 

ላለፉት ሶስት ወራት የኢሳትን ወርሃዊ ወጪ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመሸፈንና የድርጅቱን ህልውና ለመታደግ ይሆናል ብለን ያቀረብነውን የመፍትሄ ሀሳብ መነሻ በማድረግ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለጥሪያችን ዜግነታዊ ምላሽ ሰጥተዋል። የኢሳት ቦርድና ማኔጅመንት ድጋፍ ላደረጉልንና በማድረግ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ልባዊ ምስጋና ያቀርባሉ።

 

ይሁንና ኢሳትን በአነስተኛ የገንዘብ አቅም አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የሚድያ ተቋም ማድረግ አስቸጋሪና ፈታኝ መሆኑ ከማንም የተሰወረ ጉዳይ ሊሆን አይችልም። ምንም እንኳን ኢሳት የተነሳለትን አላማና ራእይ ለማሳካት እና ከዳር ለማድረስ ብዙ ጥረት እያረገ ቢሆንም፣  ከሚሰራው የስራ ብዛትና ጥራት ጋር ሲነጻጸር አሁንም በቋሚነት የወርሃዊ መዋጮ የሚያደርጉ ዜጎች ቁጥር ገና የተፈለገው ደረጃ ላይ አልደረሰም። ይህ እውነታ ደግሞ የኢሳትን ዘለቄታዊ ህልውና መፈታተኑ አይቀሬ ከመሆኑም በላይ በተለይ ኢሳት የፈነጠቀው ብሩህ ተስፋና የቀሰቀሰው የነጻነት መንፈስ ለአፍታም ቢሆን መደብዘዝ እንደማይገባው በአግባቡ የተገነዘቡ እንደ እርሶ ያሉ ኢትዮጵያዊያን በእጅጉ ሊያሳስባቸው ይችላል ብለን እናምናለን።

 

ከዚህም በመነሳት ኢሳት ያለበትን የአቅም ችግር በቋሚነት ለመቅረፍ መፍትሄ ይሆናል ብለን ያቀረብነውን፣ በትንሹ በወር $20 የአሜሪካ ዶላር በቋሚነት ድጋፍ ማድረግ ያልጀመሩ ከሆነ ዛሬውኑ ለዚህ ወሳኝ የዜግነት ጥሪ ምላሽዎን በመስጠት ኢሳትን በአስተማማኝ መሰረት ላይ ለማቆም የዜግነት ድርሻዎን ይወጡ።

 

ኢሳት ሶስት ስቱዲዎች በአምስተርዳም፣ በለንደን እና በዋሽንግተን ድሲ ያሉት ሲሆን በሀገር ቤት ደግም ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ የሆኑ ሪፖርተሮች በተለያዩ ቦታዎች አሰማርቶ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ ለመሆን በቅቷል። በአለም ዙሪያ የሚያስተላልፋቸው ፕሮግራሞች አይነትና ጥራት ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ከመሄዱም በላይ በሳተላይትና አጭር ሞገድ የሬድዮ ስርጭት፣ በድረገጽ፣ በቪድዮ እና በተንቀሳቃሽ ስልክ አማካኝነት የሚያስተላልፋቸው ስርጭቶች ለህዝብ እንዳይደርሱ የታገዱ መረጃዎችንና ነጻ ሀሳብ በማሰራጨት ላይ ይገኛል። ይህ ሁሉ የሚሰራ ስራ ከፍተኛ ወጪ እንዳለው ከማንም የተሰወረ ሃቅ አይደለም።

 

ኢሳት ወርሃዊ ወጭውን ሸፍኖ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቀጠል እንዲችል በትንሹ በወር $20 የአሜሪካ ዶላር በቋሚነት የሚከፍሉ

3750 (ሶስት ሽ ሰባት መቶ ሃምሳ) ሰዎች እንደሚያስፈልጉ ባለፈው ባወጣነው የድረሱልኝ ጥሪ ግልጽ አድርገን ነበር። ባለፈው

ወር የኢሳት ድረ-ገጽ 652,626 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺ ስድስት መቶ ሃያ ስድስት) ጊዜ እንደተጎበኘ ያለን መረጃ

ያመለክታል። በዚህም መሠረት በትንሹ በወር $20 የአሜሪካ ዶላር በቋሚነት እንዲከፍሉ የሚያስፈልጉን 3750 (ሶስት ሽ ሰባት

መቶ ሃምሳ) ሰዎች ኢሳትን በወር ከሚጎበኙት 100,000 (አንድ መቶ ሺ) ጋር በንፅፅር ሲሰላ ከ4% (ከአራት በመቶ) በታች ሲሆን፣

በአሁኑ ግዜ ደግሞ ድጋፋቸውን እየለገሱ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከእለት እለት እየጨመረ ያለ ቢሆንም የሚፈለገው ደረጃ ላይ ለመድረስ ገና ብዙ ይቀረናል። የእዚህ የንፅፅር ስሌትን ውጤት ስንመለከት፣ ሌሎች የፈለግናቸውን ታሳቢ ሁኔታዎችን አካተን ለጥሪያችን ምላሽ አለማግኘት ምክንያት ይሆናሉ ብለን ብናስብም፣ ከጎብኚው ብዛት አንፃር የሚፈለገው ቁጥር መጠን እጅግ አናሳ እንደሆነ ስናይ፣ ኢሳትን ለመደገፍ የተደረገውን ጥሪ ስኬታማ ያለመሆን ምክንያት እንቆቅልሽ ያደርገዋል።

 

እንግዲህ እርሶም፣ ኢሳት ላቀረበው የገንዘብ ድጋፍ የድረሱልኝ ጥሪ ምላሽ ላለማግኘት ምክንያት ከሆኑት መሀል አንዱ ከሆኑ፣

ዛሬውኑ በፔይፓል (PayPal) አማካኝነት፣ በዴቢት (Debit) ወይንም በክሬዲት (Credit) ካርድዎት አማካኝነት ከ$20 የአሜሪካ

ዶላር ጀምሮ በየወሩ በቋሚነት የሚቆረጥ ድጋፎትን በኢሳት ድህረ-ገጽ ላይ ዛሬውኑ ያስጀምሩ። ስለ ፔይፓል አጠቃቀም ሂደት

በቀላሉ የሚያስረዳ የቪድዮ ቅንብር በድህረ-ገጹ ላይ ተካቶ የሚገኝ በመሆኑ የአጠቃቀም ችግር የሚኖርብዎ ከሆነ እሱን

እንዲመለከቱት ከወዲሁ እናሳስባለን።

 

ፔይፓልን (PayPal) ለመጠቀም ከመረጥንባቸው ዋናዋና ምክንያቶች ውስጥ፤ ትልቅና በዚህ መሰል የክፍያ አሰባሰብ አስተማማኝ

ድርጅት በመሆኑ፣ የማንኛውንም የግል መረጃ ለሌላ ሁለተኛ አካል (ለኢሳትም እንኳን ቢሆን) አሳልፎ እነደማይሰጥ

በማረጋገጣችን እና በዓለም-አቀፍ ደረጃ ደጋፊዎቻችንን ማስተናገድ በመቻሉ ነው።

 

በመጨረሻም፣ ኢሳትን በምኞት ብቻ እንዲቀጥል ማድረግ ለማንም የማይቻል ሲሆን፣ በተግባር አስተዋጾ በማድረግ ግን ኢሳትን የምንፈልገው ደረጃ ላይ ማድረስ እንደምንችል አጠያያቂ አይደለም። ለዚህም እያንዳንዱ ነጻነት የተራበ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ስለዚህ፣ ከአምስት ደቂቃ በላይ የማይወስደውን የኢሳትን ቀጣይነት የሚያረጋግጠውን የወርሃዊ ድጋፎትን ዛሬውኑ በመጀመር ለነገው የኢሳት ህልውና ዋስትና ይሁኑ።

 

ከድሀው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚዘርፈው አንጡራ ሃብት ከፍተኛ የማፈን አቅም ከገነባው የህወሃት መራሹ ጨቋኝ ስርአት ጋር ኢሳት የሚያደርገውን ከፍተኛ ትግል መደገፍ የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ሃላፊነት መሆኑን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊዘነጋው አይገባም።

 

ለማንኛውም ቴክኒካል መረጃና ድጋፍ +1888 772 ESAT (3728) ሊደውሉ ይችላሉ።

ኢሳት የኢትዮጵያ ህዝብ ዓይንና ጆሮ ነው!!!

የኢሳት የነጻነት መንፈስ ለዘላለም ይኑር!!!