(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) የኢሕአዴግ ምክር ቤት ቀጣዪን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመምረጥ ከነገ ጀምሮ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው።
በስብሰባው የግንባሩ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር እንደሚመረጥም ተነግሯል።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ማንን ለማስመረጥ እደወሰነ ግን የተገለጸና የታወቀ ነገር የለም።
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ ስለመጠናቀቁም የተሰጠ መግለጫ የለም።
የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያካሄደውን ስብሰባ ማጠናቀቁ ይነገራል።
ስራ አስፈጻሚው ሰሞኑን ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ የግምገማ ውጤቱንና በስሩ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች የሚያቀርቧቸው የውሳኔ ሃሳቦች ለኢሕአዴግ ምክርቤት እንደሚቀርቡ ነው የተገለጸው።
የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባም ነገ ይጀምራል ተብሏል።
በዚሁም 180 አባላይ ያሉት ምክርቤት የኢሕአዴግ ሊቀመንበርንና ምክትል ሊቀመንበርን እንደሚመርጥ ይጠበቃል።የሚመረጠው ሊቀመንበርም ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖ እንደሚሰየምም ለማወቅ ተችሏል።