የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር እንደሚመርጥ አስታወቀ

(Sept. 14) የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ምክርቤት፤ በዛሬ እና በነገው እለት በአዲስ አበባ  ከተማ በሚያደርገው  ስብሰባ  የግንባሩን ሊቀመንበር እንደሚመርጥ አቶ በረከት ስምኦን አስታወቁ።

ዛሬ ተጀምሮ በነገው ዕለት በሚጠናቀቀው የምክርቤቱ ጉባኤ የሚመረጠው የኢሕአዲግ ሊቀመንበር፤ በቀጥታ የሃገሪቱ ጠ/ሚ/ር እንዲሆን ኢሕአዴግ በዕጩነት እንደሚያቀርበው ታውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ሥምኦን፤ ለአዣን ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት መግለጫ፤ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ የሚመርጠው ሰው፤ በፓርላማው ጠ/ሚ/ር ሆኖ እንዲመረጥ ኢሕአዲግ በዕጩነት እንደሚያቀርበው በትናንትናው ዕለት አረጋገጠዋል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆን የጠ/ሚኒስትርነቱን ስልጣን የፊታችን መስከረም 28/2005፤ የሚረከቡት አቶ ሃ/ማሪያም ደሳለኝ ሲሆኑ፤ ምክትል ሊቀመንበርነቱ ከሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ እንደሚሆን ቢገመትም፤ እስካሁን ድረስ የጠራ  መረጃ  የለም።