መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ሳምንት በፊት ለአጭር ቀን ስልጠና ወደ አሜሪካ ለመብረር ዝግጅታቸውን ጨርሰው ቦሌ አየር ማረፊያ የተገኙት
ምክትል ከንቲባው፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ከአገር እንዳይወጡ ተደርጓል። ዋናው ከንቲባና አንድ ባለሙያ ስልጠናውን ተካፍለው መመለሳቸው ታውቋል።
ምክትል ከንቲባው የእስልምና እምነት ተከታይ እና በኦነግ አባልነት እንደሚጠረጠሩ ምንጮች ገልጸዋል።
በከንቲባውና በምክትሉ መካከል የተፈጠረው ልዩነት እየሰፋ መምጣቱም ይነገራል።
ምንጮች እንደሚሉት ኦህዴድ ሻሸመኔ ውስጥ ያካሄደውን ግምገማ ተከትሎ በድርጀቱ አመራሮች መካከል ያለው አለመግባባት እየሰፋ ነው።