የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላልተወሰነ ጊዜያት ተራዘሙ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ የጊዜ አዋጁን ተከትሎ የሕዝብ መሰባሰብ ስጋት የፈጠረበት ገዥው ህወሃት ኢህአዴግ  የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ  ውድድሮችን ላልተወሰነ ጊዜያት ተራዘመ። በእግር ኳስ ደጋፊዎች መሃከል መንግስትን የሚቃወሙ መፈክሮች ይነሳል የሚል ስጋት ያደረባቸው የኮማንድ ፖስትቱ ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት የሚገመተው ትእዛዝን ተግባራዊ ለማድረግ የእግር ኳስ ማኅበሩ ውድድሮች እንዳይካሄዱ መርሃግብሩን አግዶታል። እስካሁን መቼ  ይጀመራሉ ለሚለው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ማኅበር በኩል መግለጫ አልተሰጠም።