የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን ገለጹ

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን ገለጹ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ከመልካም አስተዳደር፣ ከደሞዝ፣ ከማበረታቻና ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ላቀረቡት ጥያቄ የደህንነት ሰራተኞች እና ፖሊስ ድጋፋቸውን ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ በሌሎች ባለስልጣናት ታዘው የአድማ መሪዎች የተባሉ ሰዎች እንዲታሰሩ መደረጉ አስገርሟቸዋል። 120 የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የአለማቀፍ ሲቪል አቬሽን እና አለማቀፍ የሰራተኞች ድርጅት መመሪያዎች በሚፈቅዱት መሰረት ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን የሚገልጹት ሰራተኞቹ፣ ከህዳር 2010 ዓም ጀምሮ ጥያቄያዎችን በህጋዊ መንግድ ለማቅረብ ኮሚቴ አዋቅረዋል።
ሰራተኞች ነሃሴ 21 ቀን 2010 ዓም ከወታደራዊ፣ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጉዞና እና ከአምቡላስ ውጭ ሌሎች አገልግሎቶችን ለማቋረጥ ውሳኔ መወሰናቸውን ተከትሎ ፣ ከአድማው አንድ ቀን በፊት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የመገናኛ ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ የደህንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል ፖሊስ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበራራ ማሳልጠኛ ማእከል ውስጥ ሰራተኞችን ሰብስባው አነጋግረዋል።
በእለቱ የደህንነት እና የፖሊስ ሃላፊዎች የ3ቱ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት የሰራተኞችን ጥያቄዎች በአግባቡ ተመልክተው መልስ እንዲሰጡ ቢወተውቱም፣ የአየር መንገድ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተወልደ ሰራተኞችን በማስፈራራት ውትወታውን ሳይቀበለው ቀርቷል። ሰራተኞች በአቋማቸውን መጽናታቸውን ሲያዩ ባለስልጣናቱ በማስፈራሪያ ስብሰባውን የዘጉ ሲሆን፣ ነሃሴ 18 ቀን 2010 ዓም የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት ሁሉም ሰራተኞች ቀርበው አድማ እንደማያደርጉ ቃል እንዲገቡ የሚያሳስብ ደብዳቤ በትነዋል። ድርጊቱ ያበሳጫው ሰራተኞች ነሃሴ 21 አድማ ሲጀምሩ፣ ባለስልጣናቱ፣ ጠሩታ የወጡ የአየር ተቆጣጣሪዎችን፣ የአየር ትራፊክ ቁጥጥር አድርገው የማያውቁ ባለስልጣናትን፣ ከ15 አመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ስራ ያቆሙትንና በመጨረሻም በቀን 160 ዶላር እየከፈሉ የውጭ አገር የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ቀጥረዋል።
ሰራተኞቹ አገራቸውን የከዱ የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ ከተከፈተባቸው በሁዋላ 9 አስተባባሪዎች ተመርጠው መታሰራቸውን የሚገልጹት ሰራተኞች፣ ባለስልጣናቱ ሙያዊ የሆነ ውሳኔ መስጠት ሲችሉ ችግሩን በጉልበት ለመፍታት የተከተሉት አካሄድ ትክክል አይደለም ብለዋል።
ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማደናቀፍ የሞከሩና የአየር ትራፊክ ተቆጣጣዎች የስራ ማቆም አድማን ሲመሩ የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ው ለዋል።
በእስር ላይ የሚገኙት የአድማው መሪዎች ከውጭ አገር የሚመጡ አውሮፕላኖችን እንዳያርፉ ለማስተጓጎል ሞክረው እንደነበር የፖሊስ ሃላፊዎች ይናገራሉ። ይሁን እንጅ መሪዎቹ በህገመንግስት የተፈቀደላቸውን አድማ የማድረግ መብት ተነጥቀው መታሰራቸው በሰራተኞች ዘንድ ቅሬታ አስነስቷል።