መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓመታዊው የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ባሕላዊ ክብረበዓል ላይ ለሞቱና አካላቸውን ላጡ ጉዳተኞች እና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሃዘን የገለጸው ህብረቱ፣ በኢትዮጵያ የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ሁሉንም ያሳተፈ እርቅ ያስፈልጋል ብሎአል።
በዚህ በኩል ህብረቱ ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጿል። በአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ የፓርላማ አባሏ ወ/ሮ አና ጎሜዝ በኢሬቻ በአል ላይ የተፈጸመውን እልቂት በማስመልከት ለፓርላማ አባላቱ ንግግር ማቅረባቸው ይታወቃል።
በሌላ ዜና ደግሞ የአሜሪካ ኢምባሲ በኦሮምያ እየተካሄደ ካለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ዜጋው መሞቱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ በማን እንደተገደሉና የት ቦታ እንደተገደሉ አልገለጸም።