የአውሮፓ ህብረት የስዊድን ጋዜጠኞችን ለማስፈታት ጫና የሚያደርግ ከሆነ እንደማይቀበሉት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ገለጡ
ታህሳስ 21 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ለመንግስት ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የስዊድን መንግስት እስካሁን ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ ይፋዊ የሆነ ጥያቄ አለማቅረቡን ተናግረው ይሁን እንጅ የአውሮፓ ህብረት ከመደበኛው ድርድር ውጭ ጫና ለማሳረፍ ቢሞክር ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል።
የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት እና የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋማትን “መንታ ምላሶች” በማለት አቶ ሀይለማርያም ወቀሰዋቸዋል ተችተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለበት አለማቀፍ ጫና የተነሳ የስዊድን ጋዜጠኞችን ለመፍታት ቢፈልግም፣ በቅርቡ በሽብርተኝነት ክስ ከሶ ያሰራቸው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ጉዳይ ችግር እንደፈጠረበት ዲፕሎማቶችን በመጥቀስ ረዩተርስ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የ11 አመት እስራት መፍረዱ የአለም መነጋገሪያ መሆኑ ይታወቃል።
2011-12-31