ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እየከረረ በመሄዱ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በተማሪዎች ላይ ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ ተጋብተዋል ይላል የደረሰን መረጃ።
ተማሪዎቹ ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ እንዳላገኙ፣ ግቢያቸውን ለመልቀቅም ፈቃደኞች እንደልሆኑ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላትም አካባቢውን ከቦ መቀመጡን ለማወቅ ተችሎአል።
የአወልያ ኮሌጅ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በዛሬው እለት ለተለያዩ የእስልምና ተከታዮች የስልክ ጥሪ በማድረግ ለዝሁር ጸሎት እንዲቀላቀሏቸው ጠይቀዋል።
ኢሳት ቀደም ብሎ እንደዘገበው ተማሪዎች መንግስት አህባሽ እየተባለ የሚጠራውን የእስልምና አስተምህሮ መደገፉን አጥብቀው ይቃወማሉ። አንዳንድ በእምነታቸው የተነሳ ከስራ የተባረሩ መምህሮቻቸው እንዲመለሱም ተማሪዎች ጥያቄ ያቀርባሉ።