የአቶ አንዳርጋቸውን መያዝና ተላልፎ መሰጠት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዲት እናት ” እኔ ሁለት ልጆች አሉኝ፣  ልጆቼን ዛሬ ብሰጥ ደስ ይለኛል” ሲሉ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ የተሰማቸውን ስሜት በለቅሶ ገልጸዋል።

አንድ ወጣት ደግሞ እርሱና ጓደኞቹ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ወደ ትግል ፈጥነው እንዲገቡ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል።

“ቀድሞ ዘርዘሩን ዘርቷል” በሚል ቅኔ የተቀኙት አንድ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንዳርጋቸው መስዋትነት፣ ነጻነታችንን እውን እናደርጋለን ብለዋል

ሌላ ወጣት ደግሞ ” እርሱ ይህን ያክል መስዋትነት ከከፈለ እኛም እሱ የከፈለውን መስዋትነት መክፈል አለብን” ሲል ለመታገል መቁረጡን ገልጿል።

የየመን መንግስት አንዳርጋቸውን አሳልፋ በመስጠቷ ሰውነቴ በፍርሃት ሳይሆን በቁጭት እየተንቀጠቀጠ ነው የሚሉት አንድ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ “እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” ብሎ መነሳት እንዳለበት ገልጸዋል።

ህዝቡ የሚሰጠውን አስተያየት በአድማጮች አስተያየት ክፍለ ጊዜ እናቀርባለን።