ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከውጭ ጉዳይ ሰራተኞች በደረሰው መረጃ ልኡሉ በትናንትናው እለት በ2 የደህንነት ሰዎች ታጅበው ምርር ብለው እያለቀሱ ከለንደን ኢምባሴ ወጥተዋል።
የኢህአዴግ ካድሬ በመሆናቸው ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የአማካሪነት ቦታ አግኝተው የነበሩት አስራቴ ካሳ ፣ ከስራ የተባረሩት ያለ ኢምባሲው ፈቃድ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ዝግጅት ጳጳሱን በተመለከተ ቃለምልልስ ሰጥተዋል ተብሎ ነው። እርሳቸው ግን ቃለምልልሱን የሰጠሁት በአቡነ ጳውሎስ ጓደኝነት እንጅ በኢምባሲ ሰራተኛነት አይደለም በማለት ለመከራከር ሞክረዋል።
ከትናንት በስቲያ ህይወታቸው ያለፈው ብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ በመቀጥል እንደ ታማኝ ጓደኛ የሚያዩዋቸው አስራተ ካሳን ነበር።
____________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide