የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማ መጽደቅ ቢኖርበትም ላለፉት ሁለት ሳምንታት አለመቅረቡ ተገለጸ

ኢሳት (ጥቅምት 9 ፥ 2009)

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያረቀቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማ ቀርቦ መጽደቅ ቢኖርበትም አዋጁ ለሁለተኛ ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አለመቅረቡ ታወቀ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አዋጁ ለፓርላማ ቀርቦ በቀናት ውስጥ ይጸድቃል ቢልም፣ የፓርላማ አባላት በጉዳዩ ዙሪያ አለመምከራቸው ለመረዳት ተችሏል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲሱ አመት ስራውን በቅርቡ ቢጀምርም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መደበኛ የተባሉ የፓርላማ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አለመምከራቸውን የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሆነ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁ  ለፓርላማ ያልጸደቀበትን ሁኔታ በተመለከተ የሰጡት ዝርዝር መረጃ የለም።