የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ” በሰባ ደረጃ” የተሰኘው ነጠላ ዜማ “የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ” በመባል በሸገር 102 ነጥቨብ 1 የለዛ ራዲዮ ፕሮግራማ አደማጮች ተመረጠ።

መስከረም ፳፩ (ኅያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንጋፋው ድምጸዊ አለማየሁ እሸቴ ደግሞ የህይወት ዘመን ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።
ከለ380 በላይ ሙዚቃዎችን የሰራው ድምፃዊ ኣለማየሁ አሸቴ ከ ዘመናዊ ሙዚቃ ፋናወጊው ከግርማ በየነ እጅ ሽልማቱን ከተረከበ በሁዋላ ባደረገው ንግግር ፦“ምናለ ጊዜን መመለስ ብችል እና ካለፉት ጓደኞቼ ጋር ይህን ቀን ባከብረው” በማለት ብዙዎችን ስሜት ውስጥ አስገብቷል።
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በበኩሉ ፦”ሰባ ደረጃ ውስጥም፣ ሌሎች ዘፈኖቼ ውስጥም ሆነ ልቤ ውስጥ ሁሌ ያለችው ኢትዮጵያ ናት፤ ኢትዮጰያ ውስጥ ደግሞ እኛ፣እናንተ አንድ ላይ አለን፡ ከናንተ ይህን ሽልማት በማግኘቴ ትልቅ ክብር ይሰማኛል” ብሏል፦አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ሰሞኑን ለአዲስ ዓመት፣ እንዲሁም ለመስቀል በዓል አዘጋጅቷቸው የነበሩት ሁለት ኮንሰርቶች በመንግስት እንዲታገዱ መደረጋቸው ይታወቃል።
አርቲስቱ ባገዛዙ ተደጋጋሚ በደል እየደረሰበት ያለው ራሱን በፖለቲካ ሳያጠላልፍ በነጻና በገለልተኛ አቋም ስራዎቹን በመስራቱና ስሜቶቹን በመግለጹ ምክንያት እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ።
ይህ በእንዲህ ከወራት በፊት ህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ሀወሀት) የተመሰረተበትን አርባኛ አመት በደደቢት ሲያከብር የበአሉ ግንባር ቀደም አስተባባሪዎች የነበሩት አርቲስቶች ትናንት በባህርዳር በተጀመረው የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ(በአዴን) ጉባኤ ላይ የድርጅቱን መለዮ ለብሰው ከፊት ተርታ መገኘታቸውን ከስፍራው የደረሰን በምስል የተደገፈ ማስረጃ ያመለክታል።