ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ በሆነችው አረካ ከተማ የሚገኘው የገባያ ማእከል በመቃጠሉ ከፍተኛ ንብረት ወድሟል።
አብዛኞቹ ሱቆች በአቶ ሃይለማርያም የቅርብ ዘመዶችና በደኢህዴን አባላት የተያዙ እንደነበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ የእሳቱ መንስኤም የአስተዳደር በደልንና ሙስናን ከመወጋት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግምታቸውን ይገልጻሉ።
የዚህ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የአስተዳደር በደል የሚፈጸምባቸው ሲሆን፣ በተለይ ወጣቶች በአካባቢያቸው የስራ እድል እንዳያገኙ ተደርጎ አብዛኞቹ የንግድ ድርጅቶችና የንግድ ቦታዎች በአገዛዙ ሰዎች እንዲያዙ በመደረጉ ወጣቶች በተደጋጋሚ ምሬታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።