የአምባሳደር ዘውዴ ረታ የቀብር ሥነስርዓት በቅድስት ስላሴ በተክርስቲያን ተፈጸመ

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ፣ዲፕሎማትና የታሪክ ተመራማሪ የነበሩት የቀድሞ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ባለፈው ሳምንት እንግሊዝ ለንደን ውስጥ መንገድ ላይ በመውደቃቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።
አምባሳደር ዘውዴ በአዲስ አበባ ከተማ ነሐሴ 7ቀን 1927 ዓ.ም በወቅቱ ሥጋ ቤት ሠፈር ተብሎ በሚጠራውና በአሁኑ ወቅት ኦርማ ጋራዥ በሚባለው አካባቢ የተወለዱ ሲሆን የሦስት ልጆች አባትም ነበሩ።
የኤርትራ ጉዳይ፣የተፈሪ መኮንን ረጅሙ የሥልጣን ጉዞ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ታሪክ የሚሉ መጽሃፍት የጻፉ ሲሆን፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ላይ የሚያተኩረው አራተኛው መጽሐፋቸው ለሕትመት ዝግጁ እንደሆነ በድንገት በተወለዱ በ81 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።