ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ከታዋቂ የውጭ አገር ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አስተያየቶችን እኤአ ሰኔ 20 ይሰማል።
ከኢትዮጵያ የግንቦት7 ሊቀመንበር እና በበክኔል ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ እና የሶሊዳሪቲ ሙቭመንት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ሲሆን፣ ከውጭ አገር ሰዎች መካከል ደግሞ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠሪ የሆኑት የቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናል ያማማቶ ” የኢትዮጵያ የወደፊቱ ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ከመለስ በሁዋላ” በሚል ርእስ ንግግር ያደርጋሉ። በአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል አስተዳዳሪ ሆኑት ኤሪል ጋስት እንዲሁም የሚሸል አንሳሪ የአፍሪካ ሴንትራል አትላንቲክ ካውንስል ዳይሬክተር የሆኑት ፒተር ፓሃም ንግግር ያቀርባሉ።
ዝግጅቱ በቀጥታ በኢንተርኔት እንደሚተላለፍም ታውቋል።