የአሜሪካ መንግስት የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

ሰኔ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የተቀሰቀሰው የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ግጭትን አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት  ባወጣው መግለጫ ሁለቱም አገራት ከጦር ትንኮሳዎች ታቅበው በቀጠናው ዘላቂ ሰላምና መረጋት በሚሰፍንበት ጉዳይ ላይ አበክረው እንዲሰሩ ሲል  ጥሪውን አቅርቧል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በጽሑፍ ለሁለቱም አገራት በላከው መግለጫው  ሀገራቱ ከግጭት ቀስቃሽ እርምጃዎች ታቅበው ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመጡ  ጠይቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከወታደራዊ እርምጃዎች ታቅበው ጉዳዩን በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሣስበዋል።