የአማራ ክልል ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንትና የኢህአዴግ አባል የነበረው ወጣት ዘመነ ካሴ፤ ሥልጣን ላይ ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት ማስወገድ የሚቻለው በኃይል ነው በማለት ወደ ትግል ቦታ መግባቱን ለኢሳት ገለፀ።
በኢህአዴግ አባልነቱና በወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንትነቱ ቤትና መኪናን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከሥርዓቱ ሲያገኝ መቆየቱን የገለፀው ወጣት ዘመነ ካሴ፣ በሀገሪቱ በተለይ በወጣቱ ክፍል ላይ እየደረሰ ያለው ችግርና ጉስቁልና እንዲሁም ተስፋ ማጣት፣ ከሥርዓቱ ለመለየትና ሥርዓቱን ለመታገል እንደገፋው አብራርቷል።
ተመልካቾቻችን፤ ወጣት ዘመነ ካሴ፣ ወደ ትግል ለመግባት የተገፋፋበትን ምክንያት እንዲሁም በኢህአዴግ አባልነቱ ወቅት በተለይ ከወጣቶች እንቅስቃሴ አንፃር የሥርዓቱን ሚናና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ለኢሳት የሰጠውን ቃለ-ምልልስ በቀጣዮቹ ቀናት ይዘን እንቀርባለን።