የአልሸባብ ታጣቂዎች በኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት አደረሱ

 ሰኔ 28/2009

የአልሸባብ ታጣቂዎች ረቡእ ጠዋት በኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሶስት ፖሊሶች ሲገደሉ ስድስት ቆስለዋል ።

ላሙ በተባለች ሃገሪቱን ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስን መንደር በሚገኝ የኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ብዛት ያላቸው የአካባቢው ሰዎች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል ። ሰባት የሚሆኑ የፖሊስ አባላትም የደረሱበት አልታወቀም ።

ውጊያው ለ10 ሰአታት መካሄዱን ያመለከተው የቢቢሲ ዘገባ አልሸባብ ባለፉት አመታት በኬንያ ኢላማዎች ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን ጠቁሟል