ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ወኪል የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት የታሰሩ 20 ሴቶች እንዲፈቱ ዘመቻ ይጀምራሉ። ከ20 ዎቹ ሴት እስረኞች መካከል ብሌን መስፍን፣ ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንድይፍራው ከኢትዮጵያ፣ ዋንግ ያኑ፣ ጋዎ ያኑና ሊዩ ዚያ ከቻይና፣ ካጂያ ኢስማዮላ ከአዘርባጃን፣ አስቴር ዮሃንስ ከኤርትራ፣ ማትሉዩባ ካሚሎቫ ከኡዝቤክስቲያን፣ ፒዮ ፒዮ አውንግ ከበርማ፣ ሳና ሰይፍ ከግብጽ ይገኙበታል።