(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶጋን በድጋሚ ለፕሬዘዳንትነት መመረጣቸው ተሰማ።
ኤርዶጋን 53 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለቀጠዩ 5 አመታት ሀገሪቱን ለመምራት ያሸነፉ ሲሆን ተፎካካሪያቸው ሙሀራም ደግሞ 31 በመቶ የህዝብ ድምጽ ማግኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ከተቃዋሚ ወገኖች ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል እሳቤ መኖሩን ያሰፈረው የቢቢሲ ዘገባ ኤርዶጋን በስልጣን ዘመናቸው ውቅት 160 ሺ ሰዎችን ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል።
ቭላድሜር ፑቲንን ጨምሮ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሃሳን ሩሃኒ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተውላቸዋል።
የ64 አመቱ ኤርዶጋን ወደ ፕሬዝዳንትነት መንበሩ ከመምጣታቸው በፊት ለ11 አመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል።
የሃገሪቱ ህገመንግስት ለ 3ተኛ ዙር እንዲወዳደሩ ይፈቅድላቸዋል ያለው የቢቢሲ ዘገባ በቀጣይ የሚኖረው ምርጫን ጨምሮ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2028 ድረስ በስልጣን ሊቆዩ ይችላሉ የሚል ግምት መኖሩን ቢቢሲ በዘገባው አክሏል።