ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጠኝ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቅምት 11/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ፓርቲዎቹ ነጻ አሳታፊና ታአማኒ ምርጫ እንዲካሄድ በትብብር ለመስራት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በጋራ ለመታገል መስማማታቸውን ትብብር ሰነዱ ላይ አስፍረዋል።
ትብብሩን እንዲመሩ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፣ አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ ከከንባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ምክትል ሊቀመንበር፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ዋና ጻሃፊ፣ አቶ ካሳሁን አበባው ከመኢአድ ምክትል ዋና ጸሃፊ እንዲሁም
አቶ ኑሪ ሙደሂር ከመኢዴፓ ገንዘብ ያዥ ሆነው ተመርጠዋል። አንድነትና መድረክ ውስጥ የታቀፉት ፓርቲዎች ትብብሩን ለመፈረም በየድርጅቶቻቸው ውሳኔ ባለመተላለፉ አለመፈረማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ገልጾ፣ ይሁን እንጅ ፓርቲዎቹ የትብብር ስምምነቱን ይፈርማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁሟል።