የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና የእርሻ ክፍል በቅርቡ በተከሰተው ረሃብ የተጎዱ ዜጎች ሳያገግሙ በድጋሜ በጎርፍ በመጠቃታቸው ለመስከረም ወር ተጨማሪ የ3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቋል።
ድርጅቱ የኢትዮጵያን የጎርፍ አደጋ መከላከል ግብረሃይልን ጠቅሶ እንደዘገበው በጎርፉ ምክንያት 690 ሺ ተፈናቅለዋል።
55 ሺ ሄክታር መሬትም በጎርፍ መጥለቅለቁን ድርጅቱ አስታውቋል።
በድርቁ የተጎዱ ዜጎች ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ በትንሹ ሁለት አመት ያስፈልጋቸዋል።
ድርጅቱ የውሃ አቅርቦትን ለመጨመር ተጨማሪ 2 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፍልገውም ገልጿል።