የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) አቶ ተስፋዬ ጌታቸው አሜሪካ ውስጥ ህክምኛ እየተደረገላቸው በነበረበት ወቅት ማረፋቸው ታውቋል።
የአማራ ክልል የገበያ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ተስፋዬ፣ በቅርቡ ደግሞ የብአዴን ማእከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመው ነበር።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት አማካሪ እናየብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ተስፋዬ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ ከሚደግፉ እና ለውጡ ትክክለኛውን መስመር ይዞ እንዲሄድ ከሚታገሉ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ።