ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ “ፊልም የለኝም” በሚል አሳታሚዎች ተጨማሪ ወጪ አውጥተው ሌላ ማተሚያ ቤት እንዲያሰሩ የሰጠውን ትዕዛዝ አላነሳም፡፡ድርጅቱ በተጨማሪም እሁድ ዕለት የሚታተሙትን ሪፖርተር፣ፎርቹን፣ካፒታል የተባሉ ጋዜጦች የቀለም ሕትመት ማሸን ተበላሸቶብኛል በሚል ሳያትም የቀረ ሲሆን ፎርቹንና ካፒታል በዛሬው ዕለት በሁለት ቀለም ብቻ ለገበያ ሲወጡ የእሁዱ ሪፖርተር በነገው ዕለት ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የእረቡ ሪፖርተር በዚህ ምክንያት የመውጪያ ቀኑ ለዚህ ሳምንት ብቻ ወደ ሐሙስ ዕለት ተዛውሯል፡፡አሳታሚዎቹ በዚህ ያልተጠበቀ አጋጣሚ
በመቶ ሺ ብሮች የሚቆጠር ኪሳራ እንደሚደርስባቸው፣ ከማስታወቂያ ደንበኞቻቸውም ጋር ሊጋጩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡
በርካታ አሳታሚዎች የማተሚያ ቤቱ ተደጋጋሚ እርምጃ በተለይ ፈርሙ የተባለውንና ተቃውሞ የተነሳበት ውል ጉዳይ በኃላ ተባብሶ መቀጠሉ ሆን ተብሎ ነው የሚል ስሜትን ፈጥሯል፡፡ማተሚያ ቤቱ በዚህ እርምጃው ከቀጠለ ወትሮም በቋፍ ላይ ያሉ አነስተኛ አቅም ያላቸው ጋዜጦች ከገበያ ሊወጡ እንደሚችሉ እየተነገረ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት አርቅቆት ከአሳታሚዎች ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበት ውል ጉዳይ ላይ ለመወያየት በአሳታሚዎቹ በኩል የውይይት መነሻ ኀሳብ የቀረበ ቢሆንም ማተሚያ ቤቱ ለመወያየት እጠራቹሃለሁ ካለ በኃላ ለአንድ ወር ያህል ዝም ማለቱ ታውቋል፡፡የማተሚያ ቤቱ ዝምታ መራዘም ምናልባት ነገሩ እንዲቆም ወይም እንዲዘገይ ከበላይ አካል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ይሆናል የሚል ግምት አሳድሯል፡፡
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide