(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 25/2011) የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በእሳት እየተቃጠለ መሆኑ ተነገረ፡፡
4ኛ ቀኑን የያዘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ሆን ተብሎ በሰዎች የተለኮሰ መሆኑ ተነግሯል።
የእሳት ቃጠሎወን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በእሳት እየጋየ መሆኑ ታውቋል።
በፓርኩ የተከሰተው የእሳት አደጋ 4ኛ ቀኑን ይዟል።
የአደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም አደጋውን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የአደጋው መንስኤም እየተጣራ እንደሚገኝ የፓርኩ የስራ ኃላፊዎች ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ገልፀዋል ።
በፓርኩ ላይ የደረሰውን አደጋ መጠን የሚያጣራ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩ ነው የተገለጸው።
በአሁኑ ጊዚም የአካባቢው ፖሊስ ፣ መከላከያና ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀይ ቀበሮን ጨምሮ በርካታ የዱር እንስሳት የሚገኙበት መሆኑ ይታወቃል።