ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቁጥራቸው ከ2500 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ትምህርታቸውን አቋርጠው ሰልፉን የተቀላቀሉ ተማሪዎች በርካታ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
“ መንግስት የለንም፣ አገራችንን የሚመራ ሰው ይሰጠን፣ የህወሃት ድርጅት የሆነው ሳትኮን ኮንስትራክሽን ድርጅት በወረዳችን እየሰራ ያለው መንገድ ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ገንዘባችን እየተበላ ነው፣ ስራ አጥ ወጣቶች ለስደት መደረጋቸው ይብቃ፣ ወረዳችን የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ እያለ ትኩረት ሰጥቶ ባለመሰራቱ ድሆች ሆነናል፤ ብአዴን እኛን አይወክለንም፣ የኤሌክትሪክ፣ የባንክና የሆስፒታል አገልግሎቶች በወረዳችን ላይ እስካሁን ባለመሟላታቸው ትዕግስታችንን እንድንጨርስ እያደረገን ነው” የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ተስተናግደዋል።
በስራ ምክንያት ጎንደር የሚገኙት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ቀናው አሰፋ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን አረጋግጠው፣ በወረዳው የሚገኙ አመራሮች ህዝቡን ማነጋገራቸውን እና ኮሚቴ መስርተው ለማረጋጋት ሞክረዋል ብለዋል። በዳባትም በቅርቡ ተመሳሳይ የህዝብ ተቃውሞ ተካሂዶ ከ40 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸው ይተወቃል።