የቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለባቡር መስመር ሥራ በሚል (የፊታችን) ሐሙስ ከቦታው ሊነሳ መሆኑ ተገለፀ።

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የሕወሓት ንብረት የሆነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደዘገበው በ1930ዎቹ ለቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያነት የተሰራውና(አራዳ) ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ የሚገኘው ሐውልት በዚህ ሳምንት ተነስቶ ወደ ጊዜያዊ መቆያ ቦታ ይዛወራል።

 

በአዲስ አበባ በስሜን-ደቡብ አቅጣጫ ለሚሰራው የ650 ሜትር የመሬት ውስጥ የባቡር መተላለፊያ ግንባታ ምክንያት ሐውልቱ በጊዜያዊነት መነሳት አስፈልጎናል ያለው ዋልታ ሐውልቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ግቢ ውስጥ ወደተዘጋጀለት ቦታ ይዛወራል።