(ኢሳት ዲሲ–ጥር 24/2011)የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ሃውልት በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆም መሆኑ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ወጪ የተቀረጸው ሀውልት የካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ይቆማል።
ከ6 ዓመት በፊት ለጋናዊው ታላቅ መሪ ኑዋሚ ንኩሩማ በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት ውስጥ ሀውልት መቆሙ የሚታወስ ነው።
የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ሀውልት በወቅቱ ኑዋሚ ንኩሩማ ጋር እንዳይቆም የጊዜው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ድጋፍ አልሰጥም ማለታቸው ይታወቃል።