(ኢሳት ዲሲ–ጥር 16/2011)የሶማሌ ክልል መንግስት ሰሞኑን የተፈጠረውን ውዝግብ በመቆጠጣር ላይ መሆኑን አስታወቀ።
የክልሉን ፕሬዝዳንት ከስልጣን ለማስወገድ የተጀመረው እንቅስቃሴንም ማስቆሙን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በአቶ ሙስጠፋ ኡመር የሚመራውን የክልሉን መንግስት በማወክና ከስልጣን በማውረድ የቀድሞውን አገዛዝ ለመመለስ የታቀደውን ሴራ በማቀናጀት አራት የህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊና የደህንነት አዛዦች እንደሚገኙበት የሶማሌ ክልል ፕሬዛዳንት አማካሪ ለኢሳት ገልጸዋል።
ሙከራው ቢከሽፍም ተጨማሪ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስታውቀዋል።
አቶ አህመድ ሽዴ የሶማሌ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሶህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን አዲስ አበባ ጠርተው በነገው ዕለት ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ አህመድ ሽዴ ሰሞኑን በቀረበባቸው ክስ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።