የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በኦሮምያ ክልል ወረዳዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀረ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት ነሃሴ 3 ቀን 2010 ዓም በምስራቅ ሃረርጌ መዩ ወረዳ ላይ በህዝቡ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሞክረው በአካባቢው ህዝብና በኦሮምያ ፖሊስ ጥረት ከሽፏል። ተመሳሳይ ሙከራ ቁምቢ ወረዳ ላይ ተካሂዶ የነበረ ቢሆንም፣ ይህኛውም ጥቃት ሳይሳካ ቀረ። የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት አሁንም በተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት ለመሰንዘር እየሞከሩ ቢሆንም እስካሁን እንዳልተሳካላቸው ምንጮች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከ200 በላይ የህዝብ ማመላለሻና የጭነት መኪኖች በሶማሊ ልዩ ሃይል ተወስደው በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድንበር አካባቢ እንደሚገኙ ታውቋል። ንብረታቸው የህወሃት የሆኑትን መኪኖች ሳናውቅ ነው የወሰድነው በማለት መኪኖች እየተመለሱ ሲሆን፣ የሌሎች ብሄር ተወላጅ መኪኖችን ግን ታጣቂዎቹ ወስደው ማስቀረታቸውን የደረሰን መረጃ ያሳያል።
መኪኖቻቸው የተወሰዱባቸው ሰዎች መንግስት እንዲያስመልስላቸው ጥያቄ እያቀረቡ ነው።