የስቅለት በአል ተከብሮ ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 28/2010) የስቅለት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደመቀ ስነስርዓት ተከብሮ ዋለ ።

በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በዓሉ በጾም፣በጸሎትና በስግደት ተከብሮ ውሏል።

በየዓመቱ የሚከበረው የስቀለት በዓል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት እለት ነው

የእምነቱ ተከታዮች እለቱን በድምቀት ሲያከብሩት አምላክ ለሰው ልጅ የከፈለውን እዳ በማሰብ እንደሆነ ይገልጻሉ።

በመጽሀፍ ቅዱስ ኢየሱስንም ያዙት መስቀሉንም አሸክመው በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራም ወሰዱት በዚያም ሰቀሉት ይላል።

ይህንንም ተከትሎም የእምነቱ ተከታዮች  የሰው ልጅ  ድህነት አግኝቷል በማለት እለቱን በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት ያከብሩታል።

በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዛሬ የተከበረው በዓል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ስቃይና መከራ ከፍሏል በማለት መከራውንና ስቃዩን በማሰብ በየአድባራቱ በመሄድ ኪራላይሶን ወይም አቤቱ ይቀር በለን በማለት እለቱን በስግደትና በጸሎት ያሳልፉታል።