መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ30 ሺ በላይ የሚሆነው የሰቆታ ህዝብ በከፍተኛ የውሃ እጥረት የተጠቃ ሲሆን፣ ነዋሪዎች አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር ችግሩ በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ተማሪዎች ውሃ ፍለጋ ሌሊቱን ሙሉ ሲንከራተቱ የሚያድሩ ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል አልቻሉም። በአካባቢው የውሃ ወልድ በሽታም እየተዛመተ መሆኑንም ነዋሪዎች ይናገራሉ።