መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 10 የፓርቲው ሴት እና ወንድ አመራሮች ያለፉትን 11 ቀናት በእስር ቤት ካሳለፉ በሁዋላ ፖሊስ እያንዳንዳቸውን በ3 ሺ ብር ዋስ ለቋቸዋል። ምንም እንኳ አቃቢ ህግ ክስ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ የለኝም ቢልም፣ ፖሊስ እስረኞችን በነጻ ከመልቀቅ በዋስ መልቀቅን መርጧል። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃ እንደሚሉት እስረኞቹ በነጻ ካልሆነ በዋስ አንፈታም የሚል አቋም ቢይዙም፣ የፍትህ ስርአቱን መበላሸት እስካሳዩ ድረስ ትግሉን ለመቀጠል ሲባል በዋስ እንዲፈቱ ለማግባባት ተሞክሮ መፈታታቸውን ገልጸዋል
የእስር ቤት አያያዛቸውን በተመለከተ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ከኢሳት ጋር ያደረገውን አጭር ቆይታ ከዜናው መጨረሻ የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን