የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከጠቅላላ ጉባኤው ሲመለሱ ተደበደቡ

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፈቃድ በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ ላይ ተደብድበው መዘረፋቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ ጌትነት የሰማያዊን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አረካ ላይ ተደብድበው ስልካቸውንና የአንገት ሀብላቸውን ተቀምተዋል። የቀማቸው ሰው እጅ ከፍንጅ ቢያዝም ፖሊስ እርሳቸውን አስሮ ወንጀሉን የፈፀመውን ሰው ለቆታል።
አቶ ጌትነት ድርጊቱ በመንግስት የተቀነባበረ መሆኑን ገልጸው፣ አሁንም ድረስ የሚደርስባቸው ዛቻ እና ክትትል ለህይወታቸው እንደሚያሰጋቸው በመግለጽ፣ ከመሞቴ በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ ብለዋል።