ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት የኢህአዴግ አባል የሆነችው ወ/ሮ አስቴር ስዩም የወረዳው የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ፣ በቅርቡ ደግሞ በጎንደር ከተማ የጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅት ሃላፊ በመሆን ስትሰራ ቆይታለች። አስቴር የኢህአዴግ አባል ብትሆንም ከበላይ አካል የሚመጣውን ትእዛዝ ሁሉ እንደወረደ የማትቀበል እንደሆነችና በዚህም የተነሳ የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቷት እንደነበር፣ ከስራም ታግዳ መቆየቷን እርሷን በቅርብ የሚያዉቋት ይናገራሉ።
የአንድ አመት ህጻን ልጅ ትታ መታሰሩዋን የሚናገሩት ምንጮች፣ በአሁኑ ሰአት ማእከላዊ እንደምትገኝ አክለዋል።
በምእራብ አርማጭሆ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ታጋዮች የተለያዩ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ባስታወቁ ማግስት ፣ አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ተይዘው መታሰራቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።