ኀዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመረጃ ደህንነት ባለሙያዎች በማስረጃ አስደግፈው እንደገለጹት የኢህአዴግ የመረጃ ደህንነት ሰራተኞች መብራቱ በሚል ስም ኢሳት በኢንተርኔት የሚያሰራጨውን ዌብሳይት ሰብረው በመግባት፣ ጉዳት ለማድረስ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
የኮምፒዩት መለያ ቁጥሩ 197. 156. 86. 162 የሆነ አዲስ አበባ የሚገኝ ኮምፒዩተር መብራቱ በሚል የመግቢያ ስም ወደ ወደ ኢሳት ዌብሳይት ለመግባት ቢሞክርም አልተሳካለትም።
መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት የስለላ ሶፍትዌሮችን ለመጠቀም ሲሞክር መጋለጡ የአለም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የኢሳትን የቴሌቪዥን ስርጭት ለማፈን ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርጓል። ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በሁዋላ አሁን ደግሞ ተመሳሳይ ስም በመጠቀም የኢሳትን ዌብሳይት ሰብሮ መረጃዎችን ለመጥፋት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱ ገዢው ፓርቲ ከኢሳት ጋር የገጠመውን ትንቅንቅ የሚያሳይ ነው።