የመንግስት የ5 አመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ የኑሮ ውድነቱን እንዳባባሰው ተገለጠ

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚታየው የኑሮ ውድነት የታችኛውና መካከለኛ ገቢ አለው የሚባለው የመንግስት ሰራተኛው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ ነው። ጤፍ በአዲስ አበባ በኩንታል እስከ 1700 ብር በመሸጥ ላይ ነው። ዘይትና ስኳር ደግሞ ጭራሽ ከገበያ ጠፍተዋል። ለአንዳንድ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በየወሩ ስኳርና ዘይት ለማከፋፋል ሙከራ እየተደረገ ነው። እስከዛሬም መንግስት ስንዴ ከውጭ እያስመጣና ገበያውን እየደጎመ ዋጋውን ለማረጋጋት ሞክሯል። ይሁን እንጅ ትናንት የገንዘብ ሚኒሰትሩ አቶ ሶፍያን አህመድ ለፓርላማ አባላት እንደተናገሩት ይህ ሁሉ ጥረት ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ የኑሮ ውድነቱ ለመንግስት  ከባድ ራስ ምታት እና ለአገሪቱም ፈታኝ ችግር ሆኗል።

ሪፖርተር በርእሰ አንቀጹ “ኅብረተሰቡ የኑሮ ውድነቱን እስከመቼ ይሸከመዋል የሚለው ዓቢይ ጥያቄ ነው፡፡ የኑሮ ውድነት የጭነቱ ልክ ስንት ነው ለሚለው ጥያቄ የባለሙያም የመንግሥትም መልስ ይጠበቃል፡፡ አሁንም በተጨባጭ ወንጀል እየበዛ ነው፡፡ ሙስና እየበዛ ነው፡፡ ስደትና ውርደት እየተበራከተ ነው፡፡ ልመና ባህል እየሆነ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ለጠላትም መግቢያ ቀዳዳ ይከፍታልና ኋላ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በኑሮ ውድነት ምክንያት እስካሁን ሕዝባችን አልተደረመሰም፡፡ መሰነጣጠቅ ግን መታየት ጀምሯል፡፡ የጭነቱ ልክ ኅብረተሰቡ ከሚሸከመው በላይ እየሆነ ነውና ” ሲል አስጠንቅቋል።

የአዲስ አበባና በክልል ነዋሪዎች የኑሮ ውድነቱን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶችን ለኢሳት ሰጥተዋል ። አቶ ስዩም ሀጎስ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነት ህዝቡን በእጅጉ እየጎዳ እና በአንዳንድ አካባቢዎችም ማህበራዊ ቀውስ እየታየ ነው ይላሉ

አቶ ስዩም አክለውም የኑሮ ውድነቱ ህጻናትን ያለእድሜያቸው ለስራ እንዲወጡ  ሴቶችን ደግሞ ለሴተኛ አዳሪነት እየዳረገ ነው

አቶ ስዩም መንግስት የጀመረው የአምስት አመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ እንዲሁም መከላከያ ፣ የፖሊስና የደህንነት ተቋሟቱን እያሰፋ መምጣቱ ኑሮው እንዲባባስ አድረጎታል።

በደቡብ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሞሲሳ ማሞ ደግሞ በደቡብ የኑሮ ውድነቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። የመንግስት ሰራተኛው ሁሉ የቤት እቃ መሸጥ ጀምሮአል አቶ ሞሲሳ እንደሚሉት በአንዳንድ የደቡብ  ካባቢዎች ህዝቡ በረሀብ እያለቀ ነው

በአማራ ክልል ነዋሪ የሆኑት አቶ አለሁበል ማሞ በበኩላቸው የመንግስት ሰራተኛው የኑሮውን ውድነት ለመቋቋም አልቻለውም

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide