ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከአዋሳ ከተማ በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ ዛሬ በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ ሲቆስሉ ከህዝቡም በተመሳሳይ ሰዎች ቆስለዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ለእረፍት ወደ አካባቢው ከሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በመሆን፣ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር እየተወያዩ በነበረት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት ለመበትን ጥረት በማድረጋቸው ግጭቱ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ”
በግጭቱ እስካሁን በፖሊስና በህዝብ ወገን ሶስት ሶስት ሰዎች ሲቆስሉ፣ ሁለት መኪኖች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል::
ውጅግራ በሚባለው የወረዳው ከተማ 7 ሰዎች መታሰራቸውን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት መሰፈራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል ታምሩ በሻጋ፣ ሲናራ ሲዳሞ፣ አየለ፣ ዘለላምእንዲሁም ደረጃ ናስሩ የሚባሉት ይገኙበታል።
በአሁኑ ጊዜ አካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ስቱዲዮ ከገባን በሁዋላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች የደረሱን ሲሆን፣ ዘጋቢዎቻችን እስካሁን ለማረጋገጥ አልቻሉም።
ቦርቻ፣ ጭኮ እና ሌሎች አካባቢዎችም ከፍተኛ ውጥረት ይታያል። ህዝቡ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብለን አንሞትም በማለት ባገኘው መሳሪያ ሁሉ ለመከላከል መቁረጡን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚናገሩት።
በሲዳማ ዞን ከክልል እና ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ካለፈው ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ ግጭት ሲከሰት መቆየቱን መዘገባችን ይታወሳል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide